የአፋር ባህላዊ እሴቶች
አፋር በማበራዊ አኗኗሩ አኩሪ የሆነ ባህል ወግና የራሱ የሆነ ስርዓት ሲኖረው ከዘመን ሲወርድና ሲዋረድ ሳይበረዝና ሳይከለስ መሰረቱን ሳይለቅ ቱባነቱን /ኦርጅናልነቱን/እንደያዘ ያለ ነው፡፡በብዙ ዘርፍ እራሱን ከሚገልጽባቸው ሰፊ ባህሉ ለዛና ውበቱን የተላበሰ ጨዋታውን ዘፈንና ጭፈራውን እንዲሁም ከማንም ከምንም ጋር ያልተቀያጠ የራሱን አእምሮና እጅ የጥበብ አሻራ የሚመሰክር ባህላዊ የወግ እቃዎችን በመጠኑም ቢሆን እንደሚከተለው ለማስተዋወቅ እንሞክራለን፡፡
ከዚህ በታች የሚናቀርባቸው የአፋር ባህላዊ እሴቶች በአስር ክፍል የተመደቡ ሲሆን በክፍል-አንድ ባህላዊ ህግ፤በክፍል-ሁለት ባህላዊ ጭፋራዎችና ጨዋታዎች፤
ክፍል-አንድ
ባህላዊ ዘፈንና ጭፈራውየአፋር ባህላዊ አጨ ዋወት ዘፈንና ጭ ፈራው አይነቱ የበዛና የሰፋ ቢሆንም በዋነኛነት የሚ ታወ ቁት በሰርግ፤በሃይማ ኖገታዊና ማህበራዊ በአላት እድ ሜና ጾታ ን በመ ለየት እንዲሁም ሁሉም በጋራ ተሳት ፎ የሚ ያደርጉበት አንኳር የአጨ ዋወት ስልት መ ታወቂያዎች እንደሚ ከተለው ይገልጻሉ፡፡
1. ሆራ፡- ከድሮ ጀም ሮ የመ ታ ባህላዊ ዘፋን ነው ፡፡ ጨ ዋታ ዉ የሚ ጨ ወቱ ወንዶች ብዛታቸው ከስድስት ማነስ የለባቸው ም፡፡መ ጀመ ርያ ጨ ዋታ ዉን የመ ጀሚ ረው ከወንድ ነው ፡፡ አጨ ወወቱም፡-ጊሌ በቀኝ እጅ ይያዛል፤ ከዚያ እግር መ ንሳት ይ ጀም ራ ል፤የሁ ሉ ም እግር በእኩል አነሳስ አለው፡፡ እግር በጉልበት ላይ በመታጠፍ እስካ መቀመጫ ይነሳል፡፡ጨ ዋታው ወደ ጦርነት ሲኬድ ፤ በኢድ ፤በሰርግ ወዘተ ጊዜ ይጨ ዋሩታል፡፡
የሆራ ባህላዊ ዳንስ
ሰደአ፡
2. ሰደአ፡- የሚ ባለው ደግሞ ሁ ሉንም ጾታ ዎች የሚ ያሳት ፉ ቢሆንም ል ጃገረዶች ብ ቻቸው ን የሚ ጨ ፍሩበት እንዲሁም ለአካለ መ ጠ ን የደረሱና ከዚ ያም በላይ የሆኑ ግን ከጾታ ተቃራ ኒያቸው ጋር አብረው መ ጫወ ት የሚ ችሉበት የጨ ዋታ አይነት ነው ፡፡
ሰደአ፡ ባህላዊ ዳንስ
ትርትራ፡
ትርትራ፡ - የሚባለው ለጦርነት ሲሄዱና ድል አድርገው ሲመለሱ የጀግንነት ስሜት የሚገልጹበት አንድ ፉከራና ቀረርቶ ዓይነት አጨዋወት ሲሆን አብዛኛው በጎሳ ጎሳዎች በእድሜ በሰል ብለው በሚገኙ ሰዎች ዘንድ ይታወቃል፡፡
ትርትራ፡ ባህላዊ ፎከራ/ ሸለላ
ላሌ፡
4. ላሌ፡ - በመባል የሚታወቀው ጨዋታ በየትኛውም የበዓል ጊዜ የሚዘፈንና በተቀባባይ አቀንቃኝ /ዘፋኝ / እድሜ ሳይለይ ወንዶች ብቻ የሚጨፍሩበት በድምጽ በጭብጨባና በእግር ዝላይ እንቅስቃሴ ይታጀባል፡፡
ላሌ ባህላዊ ዳንስ
ኬኬ
5. ኬኬ፡- በመባል የሚታወቀው ጨዋታ በየትኛውም የበዓል ጊዜ የሚዘፈንና በተቀባባይ አቀንቃኝ /ዘፋኝ / እድሜ ሳይለይ ወንዶች ከሴቶች ጋር የሚጨፍሩበት በድምጽ በጭብጨባና በእግር ዝላይ እንቅስቃሴ የታጀበ የጨዋታ አይነት ነው፡፡
መላቦ ባህላዊ ዳንስ
መላቦ
6. መላቦ ጨዋታ ወንዶችን የሚያሳትፉ ሳይሆን ሴቶች ብቻቸውን በመሆን አብዛኛውን ጊዜ በሰርግና በኢድ በአል ጊዜ በተቀባባይ አቀንቃኝ እና በሁለት ረድፍ ተሰልፈው ጊሌ /ሰይፍ / በመያዝ እንደቦታው ስፋትና ጥበት የመዞር እንቅስቃሴ እያደረጉ የሚጫወቱበት የጨዋታ አይነት ነው፡፡
መላቦ ባህላዊ ዳንስ
ኮዕሶ
ኮዕሶከተለያዩ ጎሳዎች በተውጣጡ በሁለት ተቃራኒ ቡድኖች መካካል የሚካሄድና ጉልበትንና ትንፋሽን የሚፋታትን ሲሆን በተጨማሪም ፈጣን ሯጭ መሆን የሚፋልግ እድሜያቸው ከ 18-27 የሚገኙ ወጣት ወንዶች የሚጨወቱት የጨዋታ አይነት ነው፡፡ የጨዋታ ግዜ በበአል ቃናት፤በስርግ፤ በመኸር ወቅት ወዘተ ነው፡፡ መጨረሻ የእለቱን ጨዋታና ውድድር በመከታተል የሀገር ሽማግሌዎች አሸናፊውን ቡድን በመለየት ውጤቱን የበስራሉ፡፡
ኮዓሶ/ የአፋር ባህላዊ ኳስ ጨዋታ
ክፍል -ሁለት
የአፋር ባህላዊ አልባሳትና ጌጣ ጌጦች
የአፋር ህዝብ የራሱ የሆኔ ባህላዊ አልባሳትና ጌጣጌጦች ያሉት ሲሆን ከወረቅ፤ ከብር፤ ከነሀስ፤ ከመዳብ ፤ከዛጎልና ከስንድድ ጌጣጌጦችን በመስራት ራሱን ያስውባል፡፡ እነዚህ ጌጣጌጥ በራስ ፣በጆሮ ፣በጣት ፣በክንድ በእግር ላይ ያደርጋሉ፡፡
ሀ.ባህላዊ አልባሳት
-ኡቡኬ፤- የሴት ልብስ ሲሆን ከወገብ በታች እንደ ጉርድ የሚታጠቁት ልብስ አይነት ሲሆን ዝርግ ነው
-መስነፋ፤-የወንድ ልብስ ሲሆን እንደ ሽርጥ የሚታጠቁት ዝርግና ነጭ ከለር ያለው የልብስ አይነት ነው
-ረራይቶ፤-የወንድ ልብስ ሲሆን በትካሻ ላይ የሚደረግ ነጠላ ልብስ ነው ለ.ጌጣጌጦች
ፌራንቶ፡-/ferranto/:- ቀለበት የእጅ ጌጥ
አልቦ፡- የሴቶች የእግር ጌጥ
በጊ አሩሙ፡- ከቆዳ የተሠራ ሴቶች በወገብ ላይ የሚታጠቁት ቀበቶ ነው፡፤ ሀሌይታ፡- የሴቶች መቀነት ነው
አግቢ ከቤላ፡- የሴቶች ጫማ ኪርዶ ፡- የሴቶች አግር ጌጥ
ሀረይ ቢርታ ፡- የወንዶች የእጅ ጌጥ ሶኮይታ፡- የወንዶች የእጅ ጌጥ › ሃራይ ረጋድ ፡- የህፃናት የእጅ ጌጥ
ሶፎኑ ፡- የህፃናት አንገት ጌጥ፤ከቆዳ የተሠራ ሆኖ ጫፎቹ በስንድድ ያተዋበ ነው፡፡
ከላይ ከተጠቀሱት በተጨማሪ ወንዶች ጊሌ ፣ጩቤ በመታጠቅ ጠመንጃ ና ዱላ በመያዝ ራሣቸውን ያሰውባሉ ፀጉራቸውን ወንዶች ለማስወብ የሚጠቀሙት ከእንጨት የተሠራች ለስላሣ ቀጭን ማበጠሪያነች እርሷም ፊሌይና ትባላለች ወንዶች ለውበት ያስጌጡት ፀጉራቸው እንዳይበላሽ እንዳይተጣጠፍ ፀጉሩ የያዘው ቅባት እንደታበሳ ከእንጨት የተሠራ ትራስ ብርኩማ /ፊዴና ይጠቀማሉ ፡፡
ክፍል ሶስት
ባህላዊ የእደ ጥበብ ውጤቶች
የአፋር ሴቶች በእጃቸው ከተለያዩ ነገሮች ከቆዳ፣ከኡንጋ የተለያዩ የቤት ውስጥ መገልገያ ቁሳቁሶችን ይሰራሉ።
ኡንጋን /ዘምባባን/ የተለያዩ ቀለማት በመንከር፣ በማቅለም ለስፌት ያዘጋጁታል፣ መገልገያ ቁሳቁሶች ወብና ያማሩ እንዲሆኑ / ማድረግ ኡንጋ/ ከማማቅለማቸውም ሌላ የቆዳ ነት /ለስላሳ ቆዳ/
የተለያዩ መልክ ያላቸው ስንድዶችና ዛጎሎችን በመጠቀም ያጌጡና ማራኪ ያደረጓቸውል።
ሙዴይና እና መካሮ: የተባሉ መስፊያዎችን ለማያያዥነት ይጠቀማሉ እንጅ ሁሉም የስፌት እቃዎች ሲዘጋጁ በእጅ እንጂ ሌላ መሳሪያ አይጠቀሙም።
የአሠራራቸው ትውፈታዊ የእደ-ጥበብ እውቀትና ክህሎት ሲወርድ ሲዋረድ ቤተሰብ ቤተሰብን/እናት ልጇን በማስተማር የመጣ የእወቀት ጥበብ ነው፡፡
በአሁኑ ጊዜ ይህ ባህላዊ የእደ ጥበብ የእወቀትና ክህሎት ዘርፍ ሴቶች በማህር እየተደራጁ በተለያዩ ከተሞች ምርታቸውን እያቀረቡ ነው፡፡
በመሆኑም የአፋር ብህረሰብ የሚ ጠ ቀሙ ባቸው ዋና ዋና ባህላዊ የወግ እቃዎችን አይነታቸው እንደየ አገልግሎታቸው ከዚህ በታች እናስተዋውቃለን፡፡
የአሠራራቸው ትውፈታዊ የእደ ጥበብ እውቀትና ክህሎት ሲወርድ ሲዋረድ ቤተሰብ ቤተሰብን/ እናት ልጇን/በማስተማር የመጣ የእወቀት ጥበብ ነው፡፡
በአሁኑ ጊዜ ይህ ባህላዊ የእደ ጥበብ የእወቀትና ክህሎት ዘርፍ ሴቶች በማህር እየተደራጁ በተለያዩ ከተሞች ምርታቸውን እያቀረቡ ነው፡
፤በመሆኑም የአፋር ብህረሰብ የሚ ጠቀሙ ባቸው ዋና ዋና ባህላዊ የወግ እቃዎችን አይነታቸው እንደየ አገልግሎታ ቸው ከዚህ በታች እናስተዋው ቃለን፡፡
ለምንጣፍና ምኝታ የሚያገለግል ቁሳቁሶችወሉ /wallu/- ለመኝታ ወይንም ለምንጣፍ የሚገልግል ከከብት ቆዳ የተሰራ ነው፡፡ ሰላት ፊዶ፤- ከኡንጋ ለመስገጃ አገልግሎት የተሠራ
ዲቦራከኡንጋ የተሰራ ለግመል መጫኛ የሚያገልግል ግመሉ በሚጫንበት ወቅት ወገቡን ጭነቱ እንዳልጠው መከላከያ መደልድል /ዳውላ ነው፡፡
ፊዲማ:
ፊዲማ አገልግ ሎቱ ለመሬት ምንጣፍ የሚውል ሲሆን የሚ ሰራውም ከሰሌን /ኡንጋ ነው ፡፡ ሰሌኑ ቀለም ሳይነከርና እንዲሁም ቀለም ተነክሮ ለምንጣፍ ው በትሊሰጥ በሚችል መልኩ የተለያዩ ቅርጽ በማውጣት ይሰራል።
ፊዲማ (ምንጣፍ)
የአፋር የወተት ዕቃዎች
አፋር ብሄረሰብ የወተት መጠቀሚያ /ማለቢያና መጠጫ/ እቃዎች የተሠሩት ከእንጨት ፣ከኡንጋ ስፌት ከቆዳ ሲሆን ውበት እንዲኖራቸው ያማሩና ያሸበረቁ ለማድረግ ለፋ ቆዳ/ነት ቀለም/ ያልተነከረ የተለያዩ መልክ ያላቸው ስንድዶችና ዛጎሎች ይጠቀማሉ፡፡
አፋር ብሄረሰብ የወተት መጠቀሚያ ማለቢያና መጠጫ/እቃዎች የተሠሩት ከእንጨት፣ ከኡንጋ ስፌት ከቆዳ ሲሆን ውበት እንዲኖራቸው ያማሩና ያሸበረቁ ለማድረግ ለፋቆዳነት ቀለም ያልተነከረ የተለያዩ መልክ ያላቸው ስንድዶችና ዛጎሎች ይጠቀማሉ፡፡
አይኒ
አይኒ: ለከብቶች ማለቢያ የሚጠቀሙበት
አይኒ
ኮራ
ኮራ ከእንጨት ተጠርቦ የሚሰራ ሲሆን ይሄም ለወተት መጠራቀሚያነት ያገላግላል
ኮራ: ለወተት መጠራቀሚያነት ያገላግላል
ኮዳ /ወተት መናጫ
ይህ የወተት መናጫ ቅቤ ማውጫ ፨ እቃ የሚሰራው ከትንሽ የፍየል ግልገል በከል ቆዳ ነው፡፡
የግልገሉ ቆዳ በወተት፤ በአሬራና ከላይ በተጠቀሱት ቅጠላቅጠል ቅመሞች በውሀ ተዘፍዝፎ መሬት ውስጥ ለተወሰነ ጊዜ ይቀበራል፡፡
የቆዳው ጸጉር ይነጫል፤ በቆዳው ላየቀረው ስጋ ይነጫል ፤ በሁለቱም በኩል በውስጥም በውጭም ይነጫል፤ ይፋቃል በመቀጠልም በእጅም ሆነ በእግር ማልፋት ነው፡፡
ወተቱን ቁጭ ብለው፤ ቆመው መናጥ ሲችሉ ስራም እየሰሩ እየተንቀሳቀሱና መንገድ እየሄዱ ወተቱን ይንጣሉ፡፡
ኮዳ: ወተት መናጫ
የውሀ መጠራቀሚያ መገልገያዎች
ይህ የውሀ መያዣና ማቀዝቀዣ ከትንሽ ፍየል ግልገል ( በከል ) ቆዳ ተለፍቶ የተሰራ ነው፡፡
ብዙውን ግዜ ውሀ ለማቀዝቀዝ ሲጠቀሙበት ረጅም መንገድ ሲጓዙ ለው መያዣነት ይጠቀሙበታል፤
ረጅም መንገድ ሲጓዙ በብትራቸው /በዘንጋቸው / ጫፍ አንጠልጥለው ነፋስ እያስመቱት ስለሚጓዙ ውሀው በፍጥነት
ይቀዘቅዛል፤ በቤት / አሪ/ አካባቢም ከፍ/ ረዘም/ ካለ ቦታ ላይ ስለሚያስቀምጡት ውሀው በፍጥነት ይቀዘቅዛል፡፡
ቆዳው ውሀ ሳይጨመርበት ሲቀር ይደርቃል ይሁን እንጂ በመቆርፈድ አያበላሽም፤ምክንያቱም መጀመሪያ የተለያዩ እጽዋቶች ቅጠላ ቅጠልን
በመቀመም ተዘፍዝፎ ስለተዘጋጀ ነው፡፡
አንድ ጊዜ ቆዳው ከተዘጋጀ በኋላ ከመታጠብ በስተቀር ሌላ እንክብካቤ አይደረግለትም፡፡
ቆዳው ውሀ ሳይጨመርበት ሲቀር ይደርቃል ይሁን እንጂ በመቆርፈድ አያበላሽም፤ምክንያቱም መጀመሪያ የተለያዩ እጽዋቶች ቅጠላ ቅጠልን በመቀመም ተዘፍዝፎ ስለተዘጋጀ ነው ፡፡አንድ ጊዜ ቆዳው ከተዘጋጀ በኋላ ከመታጠብ በስተቀር ሌላ እንክብካቤ አይደረግለትም፡፡
1 ሣር/ የውሀ መቅጃ /
ይህ የውሀ መቅጃና መያዣ ከትልቅ ፍየል ቆዳ የሚዘጋጅ ነው ፡፡ሴቶች በጀርባቸው ተሸክመው ከወንዝ ፤ከኤላ፤ወ.ዘ.ተ ውሀ የሚቀዱበት ሲሆን አህያ ወይም ግመል ላይ በመጫንም ሊቀዱበት ይችላሉ ፡፡ውሀ የመቅዳት ስራ የሴቶች የስራ ድርሻ ንው፡፡
ሀ.አፍ ሌይታ፡ -ራቅ ብ ለው ሲጓዙ ደግሞ እንደ ኮዳ የሚጠቀሙበ ት የው ሃ መያዣ ከበግና ፍየል ግልገል ቆዳ የወጣ /ስልቻ/ ነው ፡፡
አፍ ሌይታ
አፍሌይታና ሣር/ውሃ ማያዣ/ለመስራት የሚጠቀሙባቸው ቅጠላ ቅጠሎች ፡-
ኮዳ: ወተት መናጫ
ራዓይሻ 2. ደባካን 3. ሣሣካ 4. ኣዳን ገሊ
እነዚህ ቅጠላ ቅጠሎች በአንድነት ተወቅጠው ለትንሽጊዜ ውሀ ጨምሮ በመዘፍዘፍ ማልፋት ነው ፡፤የቅጠላ ቅጠሎቹ ቅመም በውሀ መቅጃው በውጪም በውስጥም ነፍሳት / ባክቴሪያ ወ.ዘ.ተ / ምንግዜም እንዳይፈጥሩ ያደርጋል ፡፡ እንዲሁም ቆዳው በመቆርፈድ ተቀዶ እንዳይበላሽ ያለሰልሰዋል
o የውሀው ጣዕም እንዳይቀየር ፤ እንዳይበላሽ የማድረግ ባህሪ አለው፡፡
4.የስለት እቃዎች
ከብረት የሚሰሩ የተለያዩ አይነት የስለት እቃዎች ሲኖሩ በተለያም ለብሄረሰቡ እንደ ጦር መሳሪያ ባህላዊ ጌጥና ገመልንና የቀንድ ከብቶችን ለማረድ የሚጠቀሙበት ጊሌ /ሰይፍ / በሚል መጠሪያ ይታወቃል፡፡ይህም እንደየ አጠቃቀሙ ይለያያል፡፡
ሀ . ላክኦ ጊሌ በመባል የሚታወቀው ከጠንካራ ብረት የተሰራና ቅርጹ ከጉራዴና ከሰይፍ ለየት ያለ መሀሉ ሰፋ ጎበጥ ብሎ በሁለቱም ጎን ስለት ያለው ጫፉ ሹል ሲሆን እጀታው ከእንጨት የተሰራ ሆኖ ከብር የተሰራ ጌጣጌጥ ይለብሳል፡፡
ላክኦ ጊሌ
ለ. ታጎሪታ፡ -በመባል የሚታወቀው ከጠንካራ ብረት የተሰራና ቅርጹ ከጉራዴና ከሰይፍ ለየት ያለ መሀሉ ሰፋ ጎበጥ ብሎ በሁለቱም ጎን ስለት ያለው ጫፉ ሹል ሲሆን እጀታው ከእንጨት የተሰራ ሆኖ ሽቦ የተሰራ ጌጣጌጥ ይለብሳል፡፡
ታጎሪታ
ሌሎች የተለያዩ እቃዎችን መያዣ /ማስቀመጫዎች
ከትሆ/katho/ ከእንጨት የተሠራ ቆፊ ሲሆን ለንፍሮ ለወተት ምግብ ተፈረፍሮም ይበለበታል፡፡
ሲፋላ፡ - ከኡንጋ በተለያዩ ዲዛይንበዝርግ መልክ የተሠሩ ለግድግዳ ጌጥ፣ ለደረቅ ምግቦች መያዣና ለክዳን የሚያገለግሉ ናቸው፡፤
ሚድራ፤- ከኡንጋ ለእጣንና ለሌሎች ነገሮች መያዣ የተሠራ
ገድቦ፡- ለደረቅ ምግቦች መያዣ የሚያገለግል ከኡንጋ የተሰራ
ኦካስ፡- ከበግና ፍየል ግልገል ቆዳ የወጣ /ስልቻ/ ሲሆን ለቅቤ ወይንም ለማር መያዣ ያገለግላል፡፡
ኦካሳ
ኡዊ ሃዳ፡- ለቤት ቁሳቁሶች መስቀመጫ ማጠልጠያ ነው
ኦሊ፡- ከክብት ቆዳ የተሠራ ፣ለልብስ ወይም ሌሎች እቃዎች መያዣ /ማስቀመጫ/
ጊሪቢ፡- ከቆዳ የተሰራ አቅማዳ /ስልቻ/ ነው፡፤
ሰሮ ሀዳ፡- ልብሶችን ለማጠኒያ የሚያገለግል ከእንጨት የተሠራ ነው፡፤
የግድግዳ ጌጣጌጦች መረወሀ፡ - ከኡንጋ የተሠራ ሆኖ ከአየር ማራገቢያ ለሙቀት ማቀዝቀዣ ለግድግዳ ጌጥ የሚውል ነው ሲፋላ፡- ለግድግዳ ጌጥነትና ለሌሎች አገልግሎቶች የሚውል /ከዘንባባ የተሰራ /
Gidar sifala /ጊዳር ሲፋላ/ ለቤት ውስጥ ግድግዳ ጌጥነት የሚውል በተለያዩ ዲዛይኖች /ዚግዛግ/ቅርፅ ከዘንባባ የተሠራ ጊራ ፋኖ/Giira falu/ ;-የመሣሪያ /ጠመንጃ / ማንጠልጠያ ማስቀመጫ ሲሆን በጌጥነትም ያገለግላል በዛጎል ያሸበረቀ ነው፡፡
5.የመዝናኛ መጫዎቻዎች ፡-
ሱሲ/ዳቡዳ/ ከእንጨት የተሠራ የመጫዎቻ 20 ጉድጓዶችን /ጠጠር ማስቀመጫዎችን /የያዘ ሲሆን በግራና በቀኝ ጫፎች የጠጠሮች ማጠራቀሚያ ጉድጓዶች ያለው ነው፡፤ በመዝናናት ህብረተሰቡ ጊዜውን የሚያሳልፍበት ገበጣ ነው፡፡
ከረንቦ፡- በጭፈራና በዘፈን ህብረተሠቡ ራሱን እያዝናና የሚደሰትበት የሙዚቃ መጣሪያ ዱቤ ነው ዱቤው ከእንጨት ተሠርቶ በቆዳ የተለበጠ ነው፡፡
6.ከድንጋይ የተሠሩ እቃዎች
ሀ ኤሄይያ /ወፍጮ /፤- እናቱ ወፍጮ ተወቅሮ ተፍጣፋ ስስ ድንጋይ እንዲሆን ተደርጎ የተሠራ መጁላ ድቡል ቡል ጣፍጣፋ ያልሆነ ነው፡፤
መኩታ/ሞጎሩ/ ሙቀጫ ፡- ,ዋናው ከታች ያለው እናቱ የእንጨት ሆኖ ዘነዘናው ድብልቡል ረዘም ተደርጎ የተሠራ
ክፍል-አምስት
‹‹ፊኢማ›› የአፋር ማህበራዊ ቡድን
የሰው ልጅ መኖር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ደስታና ችግርን አብሮ በመካፈል ተረዳድቶና ተደጋግፎ ኖሯል፡፤ ይህ አብሮ የመኖር ባህሪው የሠው ልጅ በተናጠል ሊወጣው ማይችለውን ተፈጥሮአዊ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ህይወቱ ዋስትና እንዲያገኝ ስላስቻለው ማንኛውም ህብረተሰብ በቁጥር ይብዛም ይነስም በጋራ ሲሆር ይስተዋላል፡፡
አሁን ባለንበት ቴክኖሎጂ ዘመን የመረዳደቱን መንፈስ አብሮ በመኖርና በቅርበት የሚወሰን ሣይሆን አንዱ አገር ከሌላው አገር እንዲሁም አንዱ አህጉር ከሌላኛው ጋር ጊዜና ቦታ ሣይወስናቸው አንድ ላይ ለመኖር ችለዋል፡፤ የመረዳዳት መንፈስን ከአገር ደረጃ በጣም ብቅ ብለን ስንመለከት ማንም ቢሆን ከጎረቤቱ ከቤተሰቡ ወይም ከአንዱ ማህበረሰብ ክፍል ጋር የግድ መቆራኘቱ አይቀሬ ነው፡፤
ወደ ሃገራችን ሁኔታ ስንመለስ አንድ አይነት ባህልና ሃይማኖት ፆታ፣ አንድ አካባቢ መኖርና በአንድ አይነት የስራ መስክ ላይ መስማራትን መሰረት አድርጎ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተቀራርበው በመረዳደትና በመደጋፍ ይኖራል፡፡ እድር ፣ማህበር፣ጽዋ፣ ወዘተ የተለያየ ስያሜ በመስጠት
ይቀራረባሉ፡፤ አገራችን ኢትዮጲያ የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች የሚኖሩባት በመሆኗ አንድ ብሄረሰቦቿ ብዛት ባህልና ወጋቸውም የተለያየ ስለሆነ የመረዳዳትና አብሮ የመኖር ስርአታቸውም እንዲሁም የተለያየ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡
የክልሉ ማህበረሰብ በተለይ የገጠሩ ህዝብ በእለት ተእለት ኑሮው የሚገጥሙትን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለማቃለል የሚጠቀምባቸው ባህላዊ አሰራሮች ያሉት ሲሆን በደስታም ሆነ በሀዘን ፣በእርሻም ሆነ በቤት ስራ፣ በአንድ ሰው ጉልበት ሊሰራ የማይቻለውን ወይም አንድ ሠው ብቻውን ቢስራው ሊደርሰበት የሚችለውን ጉዳትና ኪሣራ በመቀነስ የጋራ ችግሮችን የሚፈታባቸውና የሚተጋገዝባቸው በውልና በአዋጅ ያልተቋቋሙ ባህላዊ ማህራዊ ህብረቶች በብዛት እንደነበሩባቸውና ዛሬም እንደሚጠቀሙባቸው ይታወቃል፡፡
ውላዊ ያልሆኑ ያላንዳች ሠነድና አዋጅ የሚደረገው ባህላዊ የመረዳደትና የመተባበር መልኮች መቼ፣ እንዴት እንደተጀመሩ ለማወቅ ጥረት ተደርጎ ትክክለኛ መልስ ለማግነት ባይቻልም እስካሁን በተገኘው መረጃ ከጥንት አባቶች ሲወርድ ሲዋረድ መጥቶ ዛሬ ለዚህ ትውልድ መድረሱን ከብሄረሰቡ አባላት ለመረዳት ተችሏል፡፡
የአፋር ብሄረሰብ የራሱ የሆነ ባህላዊና ታካዊ ስርአት ባለቤት ሲሆን ይህ የማንነቱ መግለጫ የሆነው ባህል አሁንም እንደተጠበቀ ይገኛል፡፡ የብሄረሰብን ባህል ሙሉውን ለመግለጽ በቀላሉ የሚዘለቅ ባለመሆኑ ከመነሻችን የጠቃቀስነውን የመረዳደትና አብሮ የመኖር ባህል በአፋር ብሄረሰብ ምን መልክ እንዳለው ተይቀን ያገኘነውን እናቀርባለን፡፤
አቶ ሙሳ መሀመድ ይባላሉ በአፋር ክልል ባህል ቱሪዝምና ማስታወቂያ ቢሮ የባህል መምሪያ ሃላፊ ናቸው፡፡ የአፋርን ባህል ጠንቅቀው የሚያውቁና በተለያዩ አካባቢዎች በተለያዩ የስራ መስኮች ሲሰሩ የቆዩ የሞያ ባለቤት ናቸው፡፡ የአፋርን ብሄረሰብ የእደር ስርአት የሚገልጽልን እሣቸው ናቸው፡፡
በአፋር ብሄረሰብ ባህላዊ የቡድን አደረጃጀት
‹‹ ፊኢማ›› ይባላል፡፡ ፈይህም የብርቱ ወንዶች ስብሰባ የቡድን ስም ሲሆን የፊኢማ አባላት ሠላምና
ፀጥታን የማስከበር ፣ፍርድን ማስፈፀም ፣ የታመመን የመርዳት፣እንግዳን የማስተናገድ በሰርግና በመሰል በአላት ስራ የማገዝ፣ በቀብር ወቅት መቃብሩን የማዘጋጀትና ስርአቱን ማስፈፀም ወዘተ ተግባራትን ያከናውናል፡፡ በእያንዳንዱ ጎሳበብርታታቸውና ንቃታቸው የተመረጡ ወንድ ወጣቶችና ጎማልሶች ተውጣጥተው ‹‹ፊኢማ›› ይመሰርታል፡፡
‹‹ ፊኢማ›› በመባል የሚታወቀው የአፋር ብሄረሰብ ማህበራዊ የቡድን አደረጃጀት በአንድ ሠው አቅም የማይወጡትን ስራዎች ተጋግዞ ለማቃለል ብሄረሰቡ አባላት የሚጠቁሙበት
ባህላዊ ቡድን ነው፡፤ ለስራ ተሣታዎችም ከስራ ባኋላ ባንድ ላይ መብላትና መጠጣጥም ያለ ነው፡፡
ከብሄረሰቡ ባህላዊ ማህራት መረዳዳት በችግር ጊዜ የሚፈለገውን በማዋጣት የተለያዩ ችግሮችን ለማቃለል በገንዘብ ፣በጎልበትና በምክር ድጋፎች ማድረግን ያጠቃልላል፡፤ ለመጥቀስ ያህልም ከብሄረሰቡ እጅግ ድሃ ወይም አቅም ዳካማ የሆነውን መልሶ ለማቋቋም በገንዘብና በአይነት ደጎማ ማድረግን፣ በሃዘን ወይም በቀብር ጊዜ ሃዘንተኛውን ማጽናናት፣ሃዘንተኞችን ማስተናገድና ማገልገልን ሁሉ ይጨምራል፡፡ በሰርግ ወቅትም ቢሆን ለጋብቻ የሚዘጋጀው ሰው በገንዘብ በኩል ለሚደርስበት ችግር በማዋጣት ለመፍታት የሚያገለግል አሰራር ነው፡፡
ከባድ ጉዳትና እስክ ሕይዎት መጥፋት የሚያደርጉት ግቦች በጋራ የመፍታት ፊኢማ ከቀላል እስከ በአገር ላይ ጥቃት ሲዘረዘር ለመከላከል ቅስቀሳ የማድረግ ሃላፊነትም አለበት፡፡
እንዲሁም የብሄረሰቡ አባላት የሆኑ ሴቶች ያለባቸውን የቤት ውስጥ እቃና የገንዘብ ችግር ለማቃለል አባላቱ ገንዘብ በማዋጣት በየተራ እንደ ችግራቸው ቅድሚያ እየተሰጣጡ ሁሉንም በየተራ የሚደርሣቸው የፋይናንስ የመረዳደረት ዘዴ ነው፡፤
የብሄረሰቡን አባላት በግል ለመስራት ያልቻሉትን ማንኛውም ከባድ ወይም ብዛት ላለው ስራ በዘመቻ መልክ በመስማራ የሚከናወን ባህላዊ የህብረት ስራ ነው፡፡
‹‹ ፊኢማ›› የእድር መንፈስ ቢኖረውም የአፋር ብሄረሰብ የመረዳደት ባህል ከሌሎች ብሄረሰቦች ለየት ይላል፡፡ የራሱ ባህልና ወግ አለው ፡፤ በአፋር ብሄረሰብ ውስጥ ፊኢማ ሲባል ወንድና ሴት አይቀላቀልም ወንዶች የራሣቸው ፊኢማ ሲኖራቸው ሴቶችም እንዲሁ የራሳቸው ፊኢማ አላቸውው፡ እስከ
ዛሬ ድረስ የአፋር ብሄረሰብን ባህል እድሜ የሰጠው ከጥንት አያትና ቅድመ አያቶች ጀምሮ እየተወራረሰ የመጣው የፊኢማ ባህል እንደሆነ አቶ ሙሣ ይገልፃል፡፡
‹‹ ፊኢማ›› አጠቃላይ ጽንስ ሃሣቡ በመረዳደት ላይ በመመርኮዝ በሞት፣ በሰርግና በአባላት ላይ ችግሮች ሲከሰቱ የሚከናወን ነው፡፤ በጽሁፍ የአፈረ ደንብና ስርአት ባይኖርም ከጥንት ጀምሮ በቃል ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ደንብ ለመሆኑ አቶ ሙሣ ይናገራሉ፡፡ ፊኢማ በአባላቱ እውቅና የተሠጠው አለቃ/ሰብሣቢ ይኖዋል፡፡ በስብሰቢው አማካይነት ህግና ደንብ ያልተከተለ አባል ይቀጣል፡፡ ስለዚህ አባላት ለደንቡ ተገዥ በመሆን አለባቸው፡፡
በአፋር ብሄረሰብ ብዛት ያላቸው ፊእማዎች አሉ፡፡ ማንኛውም የብሄረሰብ አባል በመረተው ፊኢማ የመግባት መብት አለው፡፤ ሆኖም ግን ከነበረበት ፊእማ ወጥቶ ወደ ሌላ ፊእማ ለመግባት ከመጀመሪያው ፊእማ ለምን እንደወጣ በቂ ምክንያት ካለቀረበ ሌለኛው ፊኢማ በአባልነት አይቀበለውም ፡፤ ቀደም ሲል እንደተገለፀው ፊእማዎች የወንድና የሴት ከመሆናቸው ሌላ አንዱን ፊእማ ከሌላው የሚለየው ባህሪ የለም ሴቶች የራሳቸው ደንብ አላቸው ወንዶቹም እንዲሁም፡፡
የሴቶች ፊእማ ላይ በማተኮር ለሰርግና ለለቅሶ ጊዜ ምን መልክ እንዳለው አቶ ሙሣን ጠይቀናቸው ነበው፡፡ ሰው በሞሞትበት ጊዜ ‹፣ፊኢማው›› ይጠራል፡፡ በዚህም ጊዜ የተለየ አለባበስ ባህል አለ ወደ ለቅሶ የሚመጡ ሴቶች ሁሉ በፀጉራቸው ላይ ሻሽ ያስራሉ ባዶ እጃቸውን አይመጡም ፡፤ ይህም የሚደረገው ሀዘንተኛውም ሆነ ዘመዶቹ ምንም አይነት ወጭ እንዳያወጡና ፊእማው ከጎናቸው መሆኑን ለማሣወቅ ነው፡
ሠርግንም በተመለከተ በፊእማዎች በኩል ጥሪ ይደረጋል በሰርግ ጊዜ ብቻ የሚዘፈን ባህላዊ ጨዋታ ይጫወታሉ፡፤ በጭፈራውም ወቅት ፊእማው
ቀድሞ ባይቸወት ሌላ ሠው መጫወት አይችልም፡፤ ቀድሞ የሚጫወት ሌላ ካለ ይቀጣል፡፡ ጨፍረው ከዘመድ አዝማድ ‹‹ፊኢማ›. ከፍተኛ ክብር ስላለው በድግሱ ወቅት ከአባላት የሚዘጋጅላቸው ምግብ የተለየ ነው፡፡ የሚሆነው፡፤
የሴቶች ፊእማ ባህልንም ከማስጠበቁ አኳያ ከፍተኛ ድርሻ ስላለው ማንኛውም የአፋር ብሄረሰብ እናት ይቀርበኛል የስማማኛል ከምትለው ፊእማ መግባት የግድ ነው ፡፡ የፊኢማ ስርአቱ ከመረዳደትና ከመደጋገፍ ባሻገር የብሄረሰቡን ባህልና ወግ የሚጠብቅ በመሆኑ ከሌሎች ባህላዊ ማህበራት የተለየ ያደርገዋል ፡፡ ፊእማ አንድ ብሄረሰብ አፋርን ብቻ የሚወክል ሲሆን ችግርንም ሆነ ደስታን የብሄረሰቡ አባላት ብቻ ተረዳድተውና ተደጋግፈው የሚወጡበት ነው፡፡ ስለዚህ በአጠቃላይ ከፊእማ ደንብ ውስ የአለባበስ ስርአቱ፣ አመጋገቡ ሰርግና ሀዘኑ እንዲሁም ማህበራዊ ተራክቦው በአባላቶቹ ዘንድ አፋርን የመምሰል ግዴታ አለበት፡፤
በአጠቃላይ ፊእማ የአፋር ብሄረሰብን ያስተሣሠረና የማንነቱ መግለጫ ስለመሆኑ አብዛኛው የብሄረሰቡ አባላት አፀንኦት ሰጥተው ነው፡፡ የሚናገሩት
፡፡ ታዲያ ይህ አኩሪ የሆነው ባህላቸው አሁንም ቢሆን በቃል ቅብብሎሽ የሚወርድ ነው፡፡ ባህሉንና ስርአቱን ጠንቅቀው የሚውቁ በእድሜ የገፋ ሰዎች ባለፋ ቁር ለተተኪው ትውልድ ይህ ባህል ሣይጓደል እንዴት ነው የሚተላለፍው የሚለው ጥያቄ መነሣቱ አይቀርም፡፡ ስለዚህ በቃል ያለ ይረሣል በጽሁፍ የሰፈረ ይወረሣል፡፡ ነውና የሚመለከታቸው አካላት ቢያስቡበት እንላለን፡፡
ዳጉ /የመረጃ ልውውጥ ዘዴ
ዳጉ በአፋር ብሄረሰብ ውስጥ ህብረተሰቡ መረጃ ለመለዋመጥ የሚጠቀምበት ዘዴ ነው፣ መረጃ ልውውጡ ከአንዱ ሰው ወደ አንዱ ሰው በቃል የሚተላለፍ ነው፡፡ ከአንድ ሰው/ሁለት ወይም በላይ /በሚገናኙበት ወቅት ስላምታ ከተለዋወጡ በኋላ የመረጃ ልውውጥ ያደርጋል፡፡ አንደኛው ወገን በመንገድ ላይ በቤት ውስጥ ወጪ ወዘተ የተመለከተውንና የሰማውን በሙሉ ይናገራል፡፡ አንድ ሣያሰቀር ውሸት /ሀሰት/ ሣይጨምር ያወራል ሌላው ቀርቶ አሁን አሁን በቴሌቪዥንና በሬድዮ የሠማውንና ያየውን ለአላየው ለልሰማው ሰው ያወራል፡፤
በመንገድ ላይ የተገናኙ አጭር መረጃ ለመለዋወጥ ከሆነ ከሰላምታ በኋላ ቆመው ይቸወታሉ፣ረዥም መረጃ ከሆነ ቂጢጥ ብለው /አረፈ ብለው/ ይጨወታሉ፡፤ ከቤት ውስጥ ከሆነ ከሰላምታ በኋላ ይጨወታሉሉ፤ ምግብ ይቀረባል ፣ከምግብ በኋላ በመቀጠል የዳጉ ልውውጥ ያካሂዳሉ በዚህ የዳጉ ልውውጥ ሀሰት የሚቸምር ሰው የለም ምክንቱም አንደኛው ወገን ተሳስቶ ቢናገር ማህበራዊ ክብሩን ያጣል ሲናገረም ይታወቅበታል፡፡ በተለይ በዳጉ ባህላዊ የመረጃ ልውውጥ ዘዴ ውሸት መናገር አጅጉን በጣም የተከለከለ በመሆኑና የሌሎች ሰወችንም ስም ሊያጎድፍና ጉዳት ሊያስክትል በመቻሉ ነው፡፡
የመረጃ ልውውጡ በአንድ ወገን ብቻ ሣይሆን በሁለተኛውም ወገን ነውው፡ በዳጉ ስነ-ስርአት መሰረት አንዱ ወገን ተናግሮ ሳይጨርስ አቋርጦ መናገር የተከለከለ ነው፡፡ የዳ ስ-ሰርአት መረጃዎችን ማቀበለና መስማት ላይ የተመሠረተ ጥሬ መረጃ ነው፡፤
በዳጉ ስነ-ሰርአት አንዱ ግለሰብ ከየት ተነስቶ የት አንደሚደርስ ለምን እንደሚንቀሳቀስ ይገልፃል፡፡ ህበረተሠቡ ከግጦሽ መሬት ውሃና ዝናብ ጋር የተያየዘ ኑሮ ስለሚኖር ተንቀሳቃሽ ነው በሚንቀሳቀስ በት ወቅት ትቶት ስለመጣው አካባቢ በጎዞው ወቅት ያጋጠሙትን ደስትና ችግሮች የሰማውንና ያየውን ስለሚሄድበት አድራሻ ሁኔታ ይገልፃል፡፡
ስለ አካባቢው ያለው እወቀት እነስትኛ ከሆነ ከሌላው ወገን መረጃ ማግኘት ይችላል፡፡ መረጃው በቤት ውስጥ ስለሚገኝ እንስሳትም ሆነ ወደ ወጪ ስለተሠማሩ የቤት እንስሳት ሁኔታ ሊሆን ይችላል፡፤ ስለቤተሰብ ጤንነት ፣ስለ ክልሉ ደህንነት ፆጥታ ፣ጦርነት፣ግጭት፣ቸለመስማማት ስለ ግለሰቦች ሁኔታም ሊሆን ይችላል ይሁነ እንጂ ሚስጥርን አይጨምርም በጥቅሉ አጠቃላይ ህይወት ሉትን ሁኔታዎች ያለምንም ፍርሀት ይለዋወጣሉ ፣ የሚንቀሳቀሱ ስለሆነ ያለምንም ጥራጣሬና ፍርሀት እውነቱን ይገልፃሉ፡፡
ከመንግስት ማስሚዲያ የሚሰራጩ ማናቸውም መረጃዎች በህዝቡ በግለሰብም ደራጃ በዳጉ ከአንዱ ወደ አንዱ ወገን ከፍጥነት የሠራጫል፡፡ ዳጉ ከህይወታቸው ጋር በጣም የተያያዘ በመሆኑ ከአንዱ ቦታ ወደ ሌላው እውነተኛ መልእክት ይተላለፋል ፣በፍጥነት ይሠራጫል፡፡
ስለዚህ ዳጉፖለቲካ ፣ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ግንኙነቶችን ለማተናከር ህብረተሠቡ የሚጠቀምባቸው የመረጃ ልውውጥ ዘዴ ነው፡፡ የሚከሰቱ ማንኛቸውንም ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች በዳጉ ይተላለፋሉ የተሰፋፋ በሽታዎች ፣ግጭት፣ዝረፈያና ስርቆት አለመስማማት የልማትና የሰላም ጉዳዮች ፣ከመንግስት ከአጎራባች ክልሎች ጋር ያሉ ግንኙነቶች ሌላው ቢቀር በግለሰብ ደረጃ ያሉ ችግሮች ወዘተ በዳጉ ሰርአት የመረጃ ልውውጥ ይደርግበታል፡፡
ስለዚህ ዳጉ መረጃ ልውውጥ ዘዴ ብቻ ሣይሆን የብሄረሰቡ ስላም መረጋገት ልማት ማስከበሪያም ዋነኛ መሳሪያ ነው፡፡ በቅጥሉ ህዝቡ ግነኙነት የመረጃ ማዕከል ነው ማለት ይቻላል፡፡
ክፍል ስድስት
የአፋር ብሔረሰብ ምግብ አዘገጃጀት /አሠራር/
የአፋር ብሔረሰብ በስፋት የተሠማራው ከዶሮ እርባታ በስተቀር የቤ ƒ እንስሳትን በማርባት ነው፡፡ አጠቃላይ ህይወቱ የተመሠረተው የቀንድ ከብቶች ፣ፍየል፣በግ፣ግመል T`uƒ ላይ ነው፡፡ የቤት እንስሳ„ቸው ¾ ምግብ፣ ¾ ገንዘብ ፣¾ ማህበራዊ ዋስትናእና ¾ ማህበራዊ ማዕ[ግ /ደረጃ/ ÁÑ“ê÷†ªM::
በገጠር የሚኖረው አርብቶ አደር ከጠቅላላው ህዝብ 86.4% ሲሆን 13.6% በከተማ የሚኖር ነው ፣ቢሆንም በከተማ የሚኖሩት ከገጠሩ ህይወት ጋር ብዙም የተላቀቁ አይደሉም፣ ክልሉ አመቱን ሙሉ የዝናብ እጥረት ስለአለበት በእርሻ ላይ የተሰማሩት ›`w„ ›Å` ቁጥር እጅግ በጣም ውሰን “†ው በመሆኑም ህዝቡ ምግቡን የሚያዘጋጀው ከሚያረባቸው ¾ ቤት እንስሳት አስተዋፅኦ ከሚገኘው ወተትና ስጋ ነው አሁን አሁን መስኖ በመጠቀም የእህል WwKA‹” እጅግ በጣም አነስተኛ uJ’ Å[Í እ Á መረቱ ÃÑ—KÁÑKÓK²? ¾T>qÓ ¾TÃuLg ’¨ÚS[¨< ÁK¨<” `Øuƒ SÖØ KTÉ[Ó“ uØ\ G<’@ SwLƒ ”Ç=‰M ’¨<::
ጥብሱ እንዲበርድ ይደረጋል ተምር ፍሬውን አውጥቶ በመለየት መጨመርና መደባለቅ መለወስ ነው፡፡ ይህ ምግብ የሚዘጋጀው ለእመጫት ለአራሶች/ ለሙሽሮችና ለህመምተኞች ለእንግዶች በቅቤና በማር መመገብም ይቻላል፡፡ ፡፤
2.5 ግንፍልታ ፡- እንስሳው ይታረዳል ፣ስጋው ይዘጋጃል ፤ይቀቀላል ፣ ጨው ጨምሮ ማብሰል ፤ይህ የሚሆነው ብዙ እንግዶች ሲጋበዙ ድንገት እንግዶች ሲመጡ የሚዘጋጀው ምግብ ነው፤፤
3 ከወተት የሚሠሩ ምግቦች
3.1 የላም ወተት ሲረጋ ይናጣል፣ ቅቤው ይወጣል /ሙቱክ/ይባላል፣ ቅቤው ተለይቶ ሲወጣ ቀሪውን አሬራ /ኢታ/ ይሉታል ከአ_ራው ላይ ወፈር ወፈር ያለውን ቅቤ መሣይ ተለይቶ ይወጣል፣ ውሃው ፈሳሹ ብቻ ይቀራል፣ ይህን ሌሞ ብለው ይጠሩታል ፣ጠሎ ከላይ የሚነሣው ደግሞ R ቦ ይባላል ለምግብነት ያገለግላል፡፡ R ቦ ቅቤ ተጨምሮበት እንደ ርጎ ይጠቀሙበታል ፡፡R ቦ ለፈታህና ለሙፌም መመገቢያ ይጠቀሙበታል፡፡ ለሁሉም ምግቦች ንፍሮን ጨምሮ ይጠቀሙበታል፡፡
3.2 G ራህ ሃን /Caxacana/ ፡- ለእንግዳ ፣ ባል ከሩቅ ቦታ ሄዶ ሲመለስ ፣ ለቤተሠብም ጭምር የሚዘጋጅ ምግብ ነው፡፡ትኩስ ወተት ይታለብና በሌላ እቃ ላይ ይገለበጣል፣ ይረጋል ፣ የተለያዩ ቅመሞች በእጅ ተፈጭተው ይጨመሩበታል፣ እንግዳው እስከ ሚመጣ ድረስ ተዘጋጅቶ ለተወሰነ
ቀናት /10 ቀናት ያህል /ይቆያል ፣እንግዳው ሲመጣ የላም ወተት ታልቦ /ትኩስ ወተት / ከረጋው እርጎ ጋር ተደባልቆ /ተጨምሮበት/ ሙፌ /ዳቦ
/ተሠጥቶት ይበላል እያማገም ሆነ እያጠቀሰ መመገብ ይችላል፡፡ ወፍራም ሰለሆነ እየተማሠለ ይ Ö ጣል
3.3 ሙራ /Murra/
የታጠነ ካኡንታ /Kaqunta /የወተት ማለቢያ እቃ /ላይ ወተት ማለብና ወዲያው ትኩሱ ወተት ላይ ማርና ቅቤ መጨመር አለበለዚያም ደግሞ ማሩና ቅቤው ላይ ወተት ማለብ፣ ይህን አዳባልቆ አዋህዶ ለወለዶች አራስ ሴት ይሠጣታል፡፡ በዚህ አይነት መንገድ አርባ ቀን ድረስ ወላዷ ትጠጣለች
፡፡ ለታመመ ሰው በተለይ በማር ይሠጣል፡፡
3.4 ጋሊ ሃን /የግመል ወተት /
የግመል ወተት እርጎ አይሆንም ፣ ተንጦም ቅቤ አ Ã ሠራለትም ሳይረጋ የሚጠጣ ወተት ነው የግመል ወተት ተጠጥቶ ውሃ አይጠጣም ሌሎች ምግቦች አይበሉም ፣ ሌላ ነገር ምንም አይቀመስም' ወሃ ጥምን ይቆርጣል፡፡ የምግብ ፍላጎት ይጨምራል ፡፡
3.5 ሪጊዳ /Riggidda/ ፡- የረጋ ላም ወተት /አዲስ የረጋ / ምንም ሳይጨመርበት ይጠጣል በዳቦም መብላት ይቻላል፡፡ ተወዳጁ ምግባችንን አዘጋጅተው ይመገቡ ይ p መሱልን
ከአፋር ባህላዊ ምግቦች መ ካከል በጥቂቱ
ክፍል -ሰባት
በክልሉ የሚገኑ ታሪካዊ ቦታዎች
የአፋር ህዝብ በራሱ ሱልጣኖችና ባላባቶች አማካኝነት ራሱን በራሱ ሲያስተዳድር የነበረ ህዝብ እንደመሆኑ መጠን በክልሉ ብዙ ታሪካዊ ቅርሶች ይገኛሉ፡፡ ከነዚህም መካከል፡-
1. አዳሌ -ጉብ ቤተ -መ ንግስት
ይህ ቤተ-መ ንግስት የሱልጣ ን መ ሀመ ድ ሀንፋሬ(ኢላልታ ) ቤተ-መ ንግሰት ነው ፡፡ ሱልጣን መ ሀመ ድ ሀንፋሬ ከ 1860-1900 ዓ.ም ድረስ መ ላው የአፋር ግዛት ሲገዛ የነበረ ሱልጣ ን ናቸው ፡፡
አዳሌ-ጉብ ቤተ-መ ንግስት
2. ገርጎሪ ቤተ -መንግስት
ይህ ቤተ -መንግስት የሱልጣን ያዮ ሲሆን ሱልጣኑ ከ 1916-1927 ኣ.ም ድረስ የነበረ ለማንም ያልተንበረካኬ ታወቂ የአውሳ ገዠ ነበሩ፡፡
ጋርጎሬ ቤተ -መንግስት
3. ገሲሰን ቤተ -መንግስት
ይህ ቤተ -መንግስት በ 1916 ዓ.ም ልጅ እያሱ በስደት ወደ አፋር ሲመጣ በወቅቱ የአውሳ ገዝ በነበረው በሱልጣን ያዮ አማካኝነት ለልጅ እያሱ መኖሪያ ተብሎ የተሰራ ሲሆን ቦሃላ የሱልጣን ያዮ ወራሽና ልጅ የነበረው ሱልጣን መሀመድ ያዮ መቀመጨነት አገልግሉዋል፡፡
ገሲሰን ቤተ-መንግስት
ክፍል-አምስት
የአፋር ብሄረሰብ ባህላዊ ጋብቻ
የአፋር ህዝብ እነደሌላው የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሠቦችና ህዝብ የሚለይበት የራሱ የሆነ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ አስተዳደራዊ ስነ-ምግበራዊ ሃይማኖታዊና ስነ ልቦናዊ ሁኔታዎችን ወይም ቋንቋ ስነ-ቃሎች ቤት አሠራር አመጋገብ ልብስና አለባበስ አጋጌጥ ከወሊድ ከሠርግና ከሞት ጋር የተያያዙ ሥርዓቶች መተጋገዝ መተሣሠብ ባህላዊ አስተዳደር ወ.ዘ.ተ ያለው ህዝብ ነው፡፡
በመሆኑም በዚህ ጽሁፍ ለመግለጽ የተፈለገው ሁሉንም የአፋር ህዝብ የማንነቱ መግለጫ የሆኑትን ባህላዊ እሴቶችን ሣይሆን ከእሴቶቹ መካከል አንዱ የሆነውን የአፋር የጋብቻ ስነ-ሥርዓትን የሚፈፀመው በብሄረሠቡ ውስጥ ከሚገኙት ጎሣዎች ለጎሣዎች ሲሆን ከአጎራባች ብሄረሠቦችና አገሮች ጋርም በጋብቻ መተሣሠር ይኖራል፡፡
በአፋር ሁለት ዓይነት የጋብቻ ስነ-ሰርአቶች አሉ እነርሱም ፡- 1 ኛ/ አብሱማ
2 ኛ/ ፋይሊ በመባል ይታወቃሉ፡፡
1 ኛ/ የአብሱማ ጋብቻ፤- ስነ ሰርአት ወንድ ልጅ ከአክስት ልጅ/ የአባቱን እህት ልጅ/ ጋር በጋብቻ የሚተሣሠርበት ስርዓት ሲሆን ሴቷ ደግሞ የእናቷን ወንድም ልጅ የምታገባበት ሆኖ ምናልበትም ከወንድምየው ወንድ ልጅ ከእህትየዋ ልጅ ባይገኝ ከእህትየዋ ሴት ልጅ ብትገኝ ከወንድምየዋ ወንድ ልጅ ቢገኝ ወይም ሌላ አጋጠሚ ቢኖር ከዚህ ከዝምድና ተዋርድ የሚቀርበው ወይም የምትቀርበው የሚጋቡበት የጋብቻ ስርዓት ነው፡፡
የአብሱማ ጋብቻ አንድ አፋር ከሌላ ጎሣ የምትመደብ የአባቱን እህት ልጅ የሚገባበት ስርዓት በመሆኑ ጎሣዎችን እርስ በርስ በማስተሣሠር አንድነትን ለመመስረት የሚደረግ ጋብቻ ነው፡፡ የአጎትና የአክስት ልጅ /cross-cousins / የሚጋቡበት የጋብቻ ስርዓት ነውው፤
ይህም በመሆኑ ማን ከማን ጋር መጋብት እንዳለበት በግልፅ የተረጋገጠ ስለሆነ ማንን አገባለሁ የሚለው ጥያቄ አሣሣቢ ጉዳይ አይደለም
አብሡማ ስያሜው ያገኘው ከዛምድና ሀረግ መጠሪያ ሲሆን ይህ ማለት ከሌላ ጎሣ የምትገኝ የአጎት ልጅ ለወንድምየው /የወደፊት ለሚሆነው
/አብሱማ ነች ስያሜው የአጎት ልጅ እንደ ማለት ይሆናል፡፡
ልጂቱን የሚያገባው አቡ በመባል ይታወቃል፡፤ ትርጉሙም አጎት እንደ ማለት ነው፡፡
የአብሱማ የጋብቻ ስነ-ሰርዓት የመብትን የግዴታ ሁኔታዎች
ስነ-ስርዓት እናት ሃላፊነት ወስዶ የማሣጨት የመዳር መብት ያላት በመሆኑ ለወንድሟ ልጅ ያለመስጠት መብት አላት ይህ ሁኔታ ከተከሠተም የዝምድና ጋብቻው በመጣሠ ምክንያት ለወንድ ቤተሰብ የሞራል ካሣ የመክፈል ግዴታ ይኖራል ጋብቻው የፈረሠው በወንድ ቤተሰብ ከሆነ የመካሳ ግዴታ የለበትም ነገር ግን የዝምድናው ሁኔታ የቀዘቀዘ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ በዚህ ምክንያት ጋብቻው እምብዛም ሲጣስ አይታይም ፡፡
አብሡማው ለማግባት የወሰን ሠው ምናልባት ልጅቷ ተፈጥሮአዊ ሆነ በሠው ሠራሽ ምክንያቶች አካልዋ ጉዳት ቢኖርባት ጤንነትዋ የተሟላ ሆኖ ባይገኝ /ድሃ ብትሆን የእድሜ ያነሰች የበለጠች /የገፋች/ብትሆን ይህን ምክንያት ተደርጎ ጋብቻውን ማፍረስ አይቻልም ሴቷም ለወንዱ ተመሣሣይ አይነት ግዴታ አለባት ፡
ስለዚህ ለአብሱማ ጋብቻ ሴቷ ወደ ፊት ትዳር አጣሎህ የሚል ስጋት አይኖራትም ፡፡ ምናልበት የወንድየው ቤተሠቦች በሌላ የተለየ ምክንያት ለጋብቻው ዝግጁ ካልሆኑ ሴቷ ከአብሡማ ወጪ ሌላ ወንድ ማግባት ትችላለች ፡፡
አንዲት ሴት በአፋር ማህበረሠብ እድሜዋ በጋብቻ ደርሳለች የሚባለው በፀጉር አሠራርዋ የመሀል አናት ላይ ፀጉር እንዳይኖራት ይደረጋል፡፡
ይህ የፀጉር አሠራርም በኮዚት ይባላል፡፡ ይህም ልጅቷ ለጋብቻ ወድረስዋን ያመላክታል፡፡ በዚህ ወቅት በአባቷ ወንድም በአጎትዋ በኩል መልዕክት የላካል፡፡ የአባት ወንድም የሌላ ከሆነ ልጁ አባቱን በመተካት መልዕክቱን እንዲያስተላልፍና ጉዳዩ እንዲጨርስ ይደርጋል፡፡ ጉዳዩ የወንዱ ቤተሠብ ከተቀበለው ለሠርጉ ዝግጂ ከሆነ የሠርጉ ሥነ-ሰርአት የሚፈጸምበት ቀንና ወር በቤተሠቡ ተወስኖ በመልዕክት ለሴቷ ቤተሠቦች ይነገራሉ፡፡ ይሁን እንጂ የአብሱማ ጋብቻ ለመፈፀም በቤት ውስጥ ያሉት ሴት ልጆች ብዙ ከሆኑ ለአቅመ አዳም ብደረሱት የበኩር ልጅ ካልተጨች ተከታዮቹ ልጆች ለእጩነት አይሠጡም፡፤
2.ፋይዲ፤- ሁለተኛው የጋብቻ አይነት ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ የአፋር የጋብቻ ሁኔታ ከማንኛውም ጎሣ ወይንም ብሄረሠብ ከዝምድና ውጪ በፍላጎት ላይ የተመሠረት የጋብቻ ዓይነት ነው፡፡ የማጨቱ ተግባራት የሚከናወነው በወንዱ ቤተሠቦች ነው፡፡ ምርጫው ከተጠናቀቀ በኋላ ወደ አጎትዋ ይላካል አጎት የወንድ ቤተሠብ ጥያቄ ተቀብሎ ለቤተሠበቿ በማሣወቅ ፍቃደኝነት በማረጋገጥ ብቻው ይከናወናል፡፤
ከላይ የተጠቀሱት የጋብቻ ዓይነቶች ለመጀመሪያ ጊዜ ትዳራቸውን ለሚመሠርቱ ተጋቢዎች የሚደረግ የጋብቻ ዓይነት ነው ነገር ግን አንዲት ሴት የመጀመሪያ ትዳርዋን አፍርሣ በሁለተኛ ጊዜ ከሌላ ሠው ጋር የሞት መሠርተው ትዳር ሀቤንቶ በመባል ይታወቃል ባልዋ የሞተባት ሴት የምትፈጽመው ጋብቻ ድግሞ ጉበና በማባል ይታወቃል፡፡
በአፋር ብሄረሠብ የጋብቻ ሥነ-ሠርአት የጥሎሽ ሂደት
የአብሱማ ጋብቻ ስርዓት ለመፈፀም የአንድ ወር ጊዜ ቀጠሮ ይያዛል ፡፡ የሴትዋ ቤት የሠርግ ወጪ የሚሸፈነው በሙሽራው ነው፡፡ በሴትዋ ቤት ከወንድያው ቤት በበለጠ ሞቅ ደመቅ ያለ ድግስ ይከናወናል፡፡ የአካባቢው ህብረተሠብና የሴትዋ ጓድኞች /የፊኢማ አባላት/ የተለያዩ ስጦታዎች ያቀርባሉ፡፡
ወንዱ ሙሽራ ጥሎሽን ጨምሮ ለሴቷ የሚሠጠው ከህፃንነቱ ጀምሮ በአባቱ ስጦታነት የተሠጠውን ንብረት በማራባት ነው፡፡ የወንዱ ጓደኞች
/የፊኢማው አባላት/ የተቻላቸውን ያህል ለድግሱ የሚሆን ፍየሎች ለድግሱ ያበረክታሉ፡፡
የአብሱማ ጋብቻ ሠርግ ስነ-ሰርአት
ለአብሱማ ጋብቻ ስነ-ሰርአት ለመፈፀም የአንድ ወር ቀነ ቀጠሮ ይያዛል የሴቷ ቤት ሠርግ ወጪ የሚሽፈነው በሙሽራው ነው ዋናው ሞቅ ደመቅ ያለው ድግስ የሚካሄደው የሚፈፀመው በሴቷ ቤት ነው፡፡ የአካባቢው ህብረተሰቡና የእርሷ ጓደኞች የተለያዩ ስጦታዎች ያቀርባሉ ወንዱ ሙሽራ ጥሎሽን ጨምሮ ለሴቷ የሚሰጠው ከህፃናቱ ጀምሮ በአባቱ ስጦታ የተሰጠውን ንብረት በማራባት ነው፡፡ ከሰርጉ ቀን አንድ ሳምንት በፊት አንስቶ በልጅቷ ቤት ጭፈራና ዘፈን ይጀመራል፡፤ ሚዚዎቹም ሙሽሪትን በዘፈን ሲያሞግሱ ሲያወድስ ያድራሉ፡፡ የዘፈን ሙገሳና ውደሳ በማግስቱም /በሠርጉ እለት/ከጠዋት ጀምሮ ይቀጥላል፡፡
የሠርጉ እለት የእህል መፍጫ ቀን ነው፡፡ ለሰርጉ የሚቀርበው የመስተንግዶ ድግስ የሚዘጋጀው በእለቱ ነው፡፡ ወንዶች ከብት አርደው በማዘጋጀት ሴቶች ድስት ጥደው በማብሰልና ዳቦ በመጋገር ይውላሉ፡፡ ከጠዋት ጀምሮ እስከ ሌሊት ሲፈጭ የታደረው ዱቄት እየተቦካ ገአንቦ ይጋገራል፡፡ ሙፌ
/ገአንቦ /የአፋር ባህላዊ ምግብ ነው፡፡ የዝግጅቱ ሁኔታ እንደ ወንዱ ሙሽራ አቅም ይወሰናል፡፡ ግመል ወይም ሌሎች አነስተኛ ከብቶች ሊታረዱ ይችላሉ፡፡ ከገአንቦ /ሙፌ ዳቦ/ በተጨማሪው ወተት፣ ቅቤ ፣ማር ያዘጋጃሉ፡፡ የአካባቢው ህብረተሰብ ተዳሚዎች የሚሰጡት ስጦታ ገንዘብ ሳይሆን ቤት ያፈራውን ገአንቦ፣ወተት፣ቅቤ፣ስኳርና ቡና ይዘው ወደ ድግስ ቤት ይሄዳሉ፡፡ ከሌለም ባዶ እጅ መሄድ ይቻላል፡፡
የአንዱ አካባቢ ከሌላው የሠርግ ስነ-ስርአት በመጠኑም ቢሆን ሊለያይ ይችላል፣ በስሜናዊ የአፋር ቦታዎች ብቸኛው የሠርግ ምግብ የሰንዴ ገንፎ ነው፡፡ በዞን አንድ አፋምቦና ዱብቲ አካባቢ የገጠር ቦታዎች ከማለዳው ጀምሮ የተዘጋጀው ዳቦ.ስጋ ወጥና ሩዝ በማዕድ በምሳ ሰአት ይቀርባል፡፤
ለግብዣ ወደ ሠርጉ የሚመጡ ተዳሚዎች የሙሽራው ጓደኞች ጭምር የመረጃ ልውውጥ/ዳጉ/ ያደርጋሉ የመረጃ ልውውጥ አንድ ሰው በመንገድ ሲሄድ /ሲመጣ/ ያለውን የሰማውን እርሱም የተናገረውን ለሌላው አዲስ ለተገናኘው ሰው መልዕክት ማስተላለፍ ነው፡፡ ይህ የመረጃ ልውውጥ /ዳጉ/ የአፋሮች ልዩ መታወቂያ ነው፡፡ መረጃ አስተላልፈው ሳይቀንስ ሳይጨምር ያለውን እውነት ያስተላልፋል ሌላው ቢቀር በአጭር ጊዜ ከቤት ወጥቶ ቢመለስ ከቤት ላልወጣው መልዕክት ያስተላልፋል፡፤
በዳጉ ስርአት ማንኛውም አፋር ከሌላ አፋር ሰው ጋር መንገድ ላይ ቢገናኝ ሰላምታ ከተለዋወጡ በኋላ የመረጃ ልውውጥ ያደርጋል፡፤ በእድሜ ታላቅ የሆነው መንገድ ላይ የተመለከተውንና ከሠዎች የሰማውን በሙሉ በዝርዝር ይናገራል፡፡ ተናግሮ ሲጨርስ በተራው የሌላኛውን መረጃ ለመስማት እየደጋገመ ነገያ ይላል ተረኛውም ተቀብሎ ነገያ እያለ ከደጋገመ በኋላ የድርሻውን መረጃ ያቀብላል፣ በዚሁ መሰረት ወደ ሠርጉ ቦታ ሲደርስ በባህሉ መሰረት የመረጃ ልውውጥ ያደርጋል፡፡
ከምሳ በኋላ የሙሽራው የቅርብ ቤተ-ዘመዶች ለብቻ ይሰባሰባሉ የሚሰባሰቡትም ምክንያት ለሙሽሪት ያዘጋጁትን ልዩ ልዩ ስጦታ ይሁን እንጂ ገንዘብም ይሰጣል፡፡ ሴት በግ ይሰጣል ይህም ኤረር ወይም አባ ሰሮ በመባል ይታወቃል፡፡ ብዙውን ጊዜ ለሙሽሪት የሚበረከተው ሰዋኒሊ 6 ክንድ ሽረጥ ሙሳን/ጥቁር ሻስ/ ጫማ ናቸው፡፡ ስጦታውን የመስጠቱን ስርአት በሙሽሪት እናት ይጀመራል፣ እናት ለሙሽሪት ካዘጋጀችላት ስጦታዎች መካከል
ከፊሉን ለታዳሚው እይታ ግልፅ በሆነ ቦታ ያስቀምጣሉ፡፡ ሙሽሪትም ፊት እንደይታይ እንደተሸፈነች ወንድሟ ተሸክሞ ወደ ታዳሚው ያመጣታል፡፤ ስጦታው እየወጣ በአይነት ይደረደራል፣ በዚህ አይነት በእናቷ የተጀመረው ስጦታ የማበርከት ስርአት በአክስቶቿ ፣በአጎቶቿና በሌሎች ቤተ-ዘመዶች አማካኝነት በየተራ ይከናወናል፡፡
የሙሽራው ሚዜዎች አጃቢዎች ሙሽራውን ከቤቱ ወደ ሙሽራው ቤት ለማምጣት ጭፈራውን እሚያደምቁበት ጊዜ ከሰአት በኋላ ነውው፤ አጃቢዎቹ ወደ ሙሽራው ስፍራ ቀረብ ካሉ ቦታ ብዙም ሳይጠጉ በመሰብሰብ ወደ ላይ እየዘለሉ አሩስ የተባለው ዘፈን በመዝፈን ይጨፍራሉ፡፡ ዘፈን ሲዘፍኑ አቀንቃኝ /መሪው/ግጥሙን እዚያው በዚያው በፍጥነት እየፈጠረ ይገጥማል፡፡ ያየውን የሚሰማውን እያወራረደ ይዘፍናል በአፋር የሚዘወተሩ የዘፈንና የዳንኪራ አይነቶች በርካታ ናቸው፡፤ የእግርና የትካሻ ፈጣን እንቅስቃሴ የሚታይበት ላሌ፣ የባላል፡፡ ሽማግሌዎች ሳይዞሩ የሚያዘወትሩት ሌላ ሁለት ተፎከካሪዎች ዙሪያውን ከበው እየዘለሉ ፈጣን የእግር ምትን ለዘብ ካለ የትካሻ እንቅስቃሴ ጋር የሚጨፈርበት ስልት ነው፡፡
ኬኬ ሚባለው ደግሞ የወጣት ሴቶች ጭፈራ ነው፡፡ ሁለት ሁለት እየሆኑ በየተራ የጨፍራል፣ ኬኬ ወደ ላይ እየዘለሉ እግሮቻቸውን እስከ መቀመጫቸው በአንዴ ማጠፍን የሚጠይቅ ጭፈራ ነው፡፡ ጭፈራው የሴቶች ቢሆንም ማስጨፈሪያው ዘፈን በወንዶች የሚታጀብበት ጊዜም አለ
፣ወንዶችና ሴቶች መስመር ሰርተው ፊት ለፊት እየተያዩ /አንጻር ለአንፃር ሆነው/ የሚያዜሙት የምሽት ጨዎታ ሰዶአ ይባላል፡፡ ሰዶ ምሽት ጨዎታ እንደመሆኑ ከአካላዊ እንቅስቃሴ ይልቅ ለዜማው ቅላፄና ለግጥሙ ይዘት ትኩረት ይሠጣል፡፤
የወንዶች ጀግና ማወደስ ጭፈራ ደግሞ ሌላ ነው፡፡ ወንዶች ስለ ጀብዲና ታላቅነታቸው ራሳቸውን የሚያወድሱበት ጭፈራውን በሁለት ዙር ክብ በመስራት ይጫወቱታል፣ በውጪው በዳር/በኩል የሚገኙት ክብ ያሉት ህብረ ዝማሬውን ሲመሩ በውስጠኛው ክብ የሚገኙት ደግሞ ማራኪ የሆነ የእግር አነሳስና አጣጣል ስልት ያሳዩበታል፡፡ በሠርግ ጊዜ ከሳምንቱ መጀመሪያ አንስቶ እስከ ሠርጉ ፍፃሜ ድረስ እንደ ሁኔታው የሚጫወቷቸው የጭፈራ አይነቶች ሌሎችንም ያካትታል፡፡
በሠርጉ እለት ከቀኑ ዘጠኝ ሰአት አካባቢ ጀምሮ ከሙሽራውቤት ብዙም ሳይራቅ ተሰብስበው የሚጨፍሩት የሙሽራው ሚዜዎችና አጃቢዎች ሙሽራውን ለማጀብ ተስማሚ የሆነውን ጭፈራ እየጨፈሩ ወደ ሙሽራው ቤት ያመራሉ፡፡ ሙሽራው ቤት ሲደርሱ የጋብቻ ስነ-ስርአት አስፈፃሚ የሆኑት የሃይማኖት አባት/መሪ/ቃዲ ቤቱ ደጃፍ ላይ በሚዘጋጀው ስፍራ የሙሽራ ልብሱን ያለብሱታል በዚህ የሰርግ እለት አዲስ ወይም አሮጌ በሚል ካልታየ በትሰቀር ከወትሮው በተለየ የሚጠቀስ አለባበስ እምብዛም የተለመደ አይደለም ፣ሴቶቹም ወንዶችም ከባህላቸው ጋር የተያየዘውን አለባበስ ይለብሳል፡፤ ብዙውን ጊዜ አዲስ ወደ ነጭ ሰምንዳ ያዘነበለ ሽረጥ ወይም ነጭ መስነፍ ሽርጥ እና ነጭ ነጠላ/ራራይቱ/ከተካሻው ላይ ያደርጋል ፀጉሩን አበጥሮ ትንሽ ጉራዴ/ጊሌ/ጠመንጃ ይታጠቃል፡፤ ዱላ/ተላተይቱ ይዞ ግራና ቀኝ በሚዜዎችና ጓደኞች ታጅቦ ወደ ሴት ቤት ይሄዳል፡፡
ልብሱን ለባብሶ እንደጨረሰ ወደ ሙሽራዋ ቤት ጉዞ ከመጀመሩ በፊት የሃይማኖት መሪው የእንኳን ደስ ያለህ ምርቃት ካደረሱ በኋላ ስጦታ የማበርከት ስ-ስርአት ይከናወናል፡፤ የገንዘቡ ስጦታ ከሙሽራው ቀኝ ትካሻ ላይ ሲነሰነስ ቀኝ ትካሻህ ይበርታ እየተባለ ይመቃል ፣በመጀመሪያ ስጦታ የሚሰጡት ወንዶች ሲሆኑ የእርሱ ስጦታ በዱአ/ፀለት/ እንደጠናቀቀ ቤተ-ዘመዶች ፣ጓደኞችና የቅርብ ወዳጆች የሆኑት ሴቶች ስጦታ ይከተላል፡፤ ከዚህ የሚቀጥለው የችፈራና የዘፈን ቸዋታ ረዘም ያለውን ጊዜ የሚወስድ ስነ-ስርአት የሆናል፡፤
አመሻሽ ላይ በአቅራቢያ ከሚገኝ ሜዳ/ገለጣ ስፍራ/ከአካባቢው የተሰበሰቡ ወጣቶች ከባህላዊ ጨዋታዎች ዋነኛ የሆነውን የኮኦሶ ጨዋታ በሁለት ተቃራኒ ቡድኖች መካከል ይካሄዳል፡፤ ከፍየል ቆዳ የተሰራውን ኳስ በመዳፋቸው በመያዝ የተቃራኒ ቡድኑን አባላት አምልጦ መሬት ላይ በማንጠር የሚፎካከሩበት ጉልበትንና ትንፋሽን በእጅጉ የሚፈታን /የሚፈታተን/ የጨዋታ አይነት ነው፡፡
የኮኦሶ ብርቱ ፋክክር እንደተጠናቀቀ ሙሽራው በአጃቢዎቹና ሚዜዎቹ ታጅቦ ወደ ሙሽራዊ ቤት ይሄዳል፡፡ እቤቱ ሲቀርብ ሆነ የተባለውን የባህል ጨዋታ እየጨፈሩ ቤት ይደርሳሉ ከደጃፍ ሲደርሱ መብሉድ ነቢዩ መሀመድ /ሱ.አ.ወ/ እወደሱ የጨፍራሉ፡፡ በዚህን ወቅት ጠመንጃ የያዙ ወደ ላይ እየጠኮሱ ወደ ቤቱ ይቀርባሉ እቤቱ ይገባል፡፡ ሙሽራው አልጋ ላይ ይቀመጣል ፣ቀጣዩ ስነ-ሰርአት ኒካ ወይም ሰሚኒ ቃል-ኪዳን ማሰር ይሆናል፡፡ ከሙሽራው ጋር ወደ ሴቷ ቤት የመጡት የሃይማኖት አባት ስነ-ሰርአት ይፈፀማሉ፡፡ የኒካው ስርአት ሲጀመር የሙሽሪት አጎት ሙሽሪት ወደ ምትገኘበት በመግባት ፈቃደኝነቷን ጠይቆ ይመለሳል፡፤ ጋብቻ አስፈፃሚው /የሃይማኖት መሪው /የአጎቷን መልስ ከሰሙ በኋላ ፈቃደኝነት መሆኗን ለተሰበሰው ታዳሚ በይፋ ያሳውቃሉ፡፡ ጠመንጃ ቀጥሎ ወደ ሰማይ ይተኮሳል፣ ኒካ እንደተፈፀመ የተሸፋፈነው የሙሽሪት ፊት ይገለጥና መልካም መአዛና ሽታ
ባለው ጢስ ትታጠናለች ከጥቂት ሠአታት በኋላ ከዋናው ቤት ተሸክመው ወደ ጫጉላው ቤት ይወስዷታል፡፡ እዚያም ከሙሽራው ጎን ትቀመጣለች ሙሽራውና ሙሽሪት ከዚያ ስአት ጀምሮ አርሷ ቤተሰቦች አቅራቢያ ከተዘጋጀላቸው የቸጉላ ቤት ለሰባት ቀናት ያህል ይቆያሉ፡፤ ከሰባተኛው ቀን በኋላ ሙሽራው ሙሽሪትን ትቶ/ብቻዋን/ብቻውን ወደ እርሱ ቤት ቤተሰቦች ቤት ይሄዳል፡፡
በሚቀጥሉት ሰባት ቀናት ውስጥ የሴትነት የባለትዳርነት ምልክት ከሆኑት የፀጉር ስራዎች መካከል ውስ አንድን የፀጉር አሰራር በመ ም ረጥ ተስራለች፡፡
እንዲሁ ም ጥሩ ሽታ እንዲኖራት አነስተኛ ጠባብ ጉድጓድ በመቆፈር ተሸፋፍና ጢ ስ ትሞቃለች ፣በአጠ ቃላይ በነዚህ ቀናት ከልጀገረድነት ወደ ወ/ሮ የምትሽጋገርበት ጊዜ ነው የራ ሷ ፀጉር ሰሬት ሙ ለው ን ክቡን ይደፍናል፡፡
ሴቷ ጢ ስ ስትሞቅ መ ጀመ ሪያ ገለዋን ፀጉሯን ትታጠ ባለች የበግ ፣የፍየል ወይም ላም ቅቤ የተገነው ን ትቀባለች ዳይታ /ሞ ራ/አድሬ
፣ ኡዱ ፣የአደስ ቁኒ፣አክባኒ/አብሽ/ቦቦኦ ተፈጭ ቶ ትቀባለች ፣ከእንጨ ት አይነት አዳይቱ፣ኪላይቱ ፣መ ደሬ፣በሬ ሂኔታ ፣ኩስራና ቦቦኦ ወዘተ በተስራው ትንሽ ጉድ ጓድ ያአዱ ቦዶ ው ስጥ በእሳት ተያይዞ የሚ ወጣ ው ጢ ስ ላይ ሰው ነቷ ተሸፋፍኖ ጢ ሱ እንዳይወጣ በደንብ ተደርጎ ተቀምጦ ትሞ ቃለች፣ ይህንም ያአዱ ብ ለው ይጠ ሩታል፡፡
በሚ ቀጥሉት ቀናት ከአንድ ወር ያህል ሙ ሽራው ወደ ቤተሰቦቹ ቀን ቀን እየሄደ ማ ታ ማ ታ ወደ ሴቷ ይመ ለሳል፡፤ በመ ቀጠል ለአንድ ወር ያህል ከሴቷ ቤት መ ዋል ይጀምራል፡፡ በሦስተኛው ወር ላይ እናቷ ቤተሰቦች ጋር ቤት ይሰራላቸዋል፡፡ በአንድነት መኖር ይጀም ራሉ፡፤ ቤቱ ሲሰራ ለስራው የሚ ያገለግሉ ኦንጋ ሴናንቱ/ዲቦራ/አሎ ይታ/የባህል አልጋ ባል ይዞ ይመ ጣል፣ቀሪው የቤት መ ስሪያ በእርሷ ቤተሰቦች ይሆናል፡፡
እናቷ የኑሮ ሁኔታን ታስተም ራለች ለእርሷም ሆ ነ ለባሏ የሚ ሰሩ ስራዎችንና አስፈላጊ ነገሮችን እየተማ ረች ከእናቷ ጋር አንድ አመ ት ትቆያለች በዚህ አንድ አመ ት ጊዜ ው ስጥ ምግብ ዝግጅት በአንድነት ከእናቷ ጋር ነው ፡፡
ከዚያ በኋላ ባል ልው ሰድ ካለ ወደ ሚ ፈልግበት ቦታ መ ሄድ ይችላሉ፡፤ ባል እናት ከሌለው የሴ ቲቷ ልጅ እናት አክስቱ/ብቸኛ መሆኑን በማ ወቅ የወንድሟ ልጅ በኑሮው እንዳይጎዳ ከሰርግ እለት በኋላ ወደ ባል ቤት እንድትሄድ ልትፈቅድ ተችላለች ፡፡
ወደ ባል ቤተሰብ መ ንደር ሲጓዙ መ ንገድ የም ትመ ራው የልጅቱ እናት ቅርብ ዘመ ድ የሆነች ባልቴት ነች በዚህ ወቅት ወደ ባሏ ቤተሰብ ስትሄድ ቤተሰቧ ስጦ ታ ያበረክቱለታል፡፤ ስጦታው ን አፋይቶ ይሉ ታል፡፤ ይህም ስጦታ ባለቸው አቅም መ ጠ ን ፍየሎ ች በጎች ላሞ ች ከቻሉ ግመ ሎ ች ናቸው ፡፤ ይህም በወንድ ቤተሰብ ፊት የኔ ነው ብ ላ /ንብረቱ/ምትለው እንዲሆ ን ነው ፡፤ ከወንዱ ቤተሰብ ወይም ከባሏ ጋር አለመ ስማ ማ ት ቢፈጠ ር ለራሷ ም ትወስደው ነው ፡፤
ጓደኞቿ ከቤተሰቦቹ ቤት ሲደርስ ቤቷን ይሰሩላታል፡፤ ለማገዶና ለመ ብራት የሚ ው ል እንጨ ት ሰብረው ያመጡ ላታል፡፤ ቤት ው ስጥ የሚ ያስፈልጉ ዝግጅቶችን ያዘጋጃሉ፣ በመ ቀጠል ጓደኞቹ ወደ ቤተሰቦቻቸው ይመ ለሳሉ፡፡