የአፋር ማድዓ
ዲጂታል የንባብ ሁኔታ
መግቢያ
የአፋር ባህላዊ ሕግ "ማድዓ" ለዘመናት በቃል ሲተላለፍ የቆየ፣ ከጋብቻና ውርስ እስከ ከባድ ወንጀሎች እንዲሁም የተፈጥሮ
ሀብት (ውኃና ሳር) አጠቃቀም ድረስ ሁሉንም የሕይወት ዘርፎች የሚገዛ ሁሉን አቀፍ ስርዓት ነው፡፡
እነዚህ ባህላዊ ህጎች ከነበሩበት ሰብስቦ በበጽሁፍ ማስቀመጥ አስፈለገ፡፡
የመሰባሰቡ ሂደት በሁለት አይነት መንገድ የተካሄደ ሲሆን ይህም ለ7 ተከታታይ አመታት ተካሂዷል፡፡
ይህም ከ2000 ዓ.ም እስከ 2006 ዓ.ም ድረስ ነበር፡፡
አምስቱ የአፋር ባህላዊ ህጎች
1. ቡርዒሊ ማድዓ
ይህ የማድዓ ህጉ አይነት: በኤርትራ ውስጥ ኢዲ በተባለ ቦታ ሊዩ ስሙ ማድዓህ ኣላይቶ (የህግ አላይቶ/ዛፍ) በተባለ ቦታ የተነደፈ ሲሆን
በኤርትራ፣ በአፋር ክልል ዞን 2 እና ዞን 4 አከባቢዎች አግልግሎት ላይ ይውላል።
በዚህ የማድዓ አይነት አብዛኛው ካሳ የሚተመነው በፍየል ነው።
2. ቡዲቶ ባዲህ ማድዓ
ይህ የማድዓ ህጉ አይነት:
ሞጎሮስና ዳቡ መካከል በሚገኝ ረኩብ ሀዳ በተባለ ቦታ የተነደፈ
ሲሆን በኤርትራ፣ በኢትዮጺያ አፋር ክልል 1 አንድ፣ ዞን 3፣ ዞን 4 አራትና ዞን 5 አከባቢዎች አግልግሎት ላይ ይውላል።
በዚህ የማድዓ አይነት አብዛኛው ካሳ የሚተመነው በግመል፣ በከብትና ፍየል ነው።
3. አፍኪዐክ ማዓዲህ ማድዓ
ይህ የማድዓ ህጉ አይነት: ከአይሳኢታ ዋላዓሳን በተባለ ቦታ የተነደፈ ሲሆን በአፋር ክልል ዞን 1፣ ዞን 3 እና ዞን 5 አከባቢዎች አግልግሎት ላይ ይውላል።
4. ባዶይታ መላህ ማድዓ
ይህ የማድዓ ህጉ አይነት: አዳአር ወረዳ ቴውኦ በተባለ ቦታ የተነደፈ ሲሆን በአፋር ክልል ዞን 5 አከባቢዎች አግልግሎት ላይ ይውላል።
5. ዴብኔክ ዌኢሚህ ማድዓ
ይህ የማድዓ ህጉ አይነት: በዌኢሚ ወንዝ አዳይሉ በተባለ ቦታ የተነደፈ ሲሆን በጅቡቲና አፋር ክልል ዞን 3 አካባቢ አግልግሎት ላይ ይውላል።
የባህላዊ ህጉ ምንነትና ባህሪያት
የአፋር ባህላዊ ህግ ትርጉም ሲንመለከት የቅጣት ውሳኔ የሚወሰነው በሁለት መሰረታዊ ነገሮች ላይ ነው፡፡
እነሱም "የተከላከሉ ነገሮች ፈጽሞ መገኝትና ፈጽም የተባሉት ነገር ፋጽሞ አለመገኘት" ናቸው፡፡
ልዩ ባህሪያት
- አጥፊው ሳይያዝ ወይም ሳይታሰር መቅጣት መቻሉ
- አውቆ መፈጸሙና ሳያውቅ መፈጸሙን ለይቶ መቅጣት
- ጥፋት መፈጸሙን እያዩ ያለመከልከል (እያዩ ማለፍ) ያስቀጣል
- አጥፍው ብቻ ሳይሆን የአጥፊው ጎሳ በሙሉ ተጠያቂ የሚያድርግ የጋራ ሃላፊነትና ተጠያቂነት የሚጥል መሆኑ
- የፍርድ ሂደቱን ከህጻናትና ሴቶች በስተቀር ማንኛውም ሰው ችሎቱን መታደም ወይም ሀሳብ መስጠት ይችላል
- ካሳ በእንስሳት ይከፈላል (ህይወት ባለው በእንስሳት እንጂ በገንዘብ አይደለም)
የአፋር ባህላዊ ህግ የፍርድ ሂደት (ሸንጎ)
- አቤቱታ ይቀርባል።
- አቤቱታ አቅራቢው ትልቅ ሰው ከሆኔ የፍርድ ይወሰናል፡፡
ልጅ ከሆኔ ቀን ደግሞ ዋስ/ተጠሪ አምጣ ይባላል፡፡ - ለቀረበው አቤቱታ ቀን ይቆረጣል፡፡
- ለተቆረጦው ቀን የችሎት(ሸንጎ) የሚደረግበት ቀንና ቦታ ይሰየማል፡፡
- ሽንጎ ሲቀመጡ ምግብና ውሃ አቤቱታ አቅራቢው/ዎቹ እንድሸፍን ይደረጋል፡፡
- ችሎቱ (ሽንጎ) ከመጀመራቸው በፍት ከከሳሹም ሆኔ ከተከሳሽ ዋስ እንድያቀረቡ ይጠየቃሉ፡፡
- የመናገር እድሉን በመጀመሪያ ለአቤቱታ አቅራቢዎች ይሰጣል፡፡
- ቀጥሎ እምነት-ክደት ቃላቸውን እንድሰጡ ለተከሳሽ ወገን እድል ይሳጣል፡፡
- ዳግመኛ የመናገርእድል ለሁለቱም ወገን ይሳጣል፡፡
- የተባለው እንደዚህ ነው ወይ? በማለት ስለተደረገው ክርክርጭብጡን አጠር ባለ መልኩ ይከለሳል፡፡፡
- የክርክሩን ጭብጥ በመገምገም ይተናትኑታል፡፡
- የተደረገው ክርክር ምስክር አስፋልጉዋል ወይስ በእነሱ ንግ ግር ብቻ ተቆጨ? ተብሎ ይመረመራል።
- ክርክሩ ምስክር ከሳፈለገ የምስክሮች ቃል ይደመጣል፡፡
ምስክሮቹ በቦታው ከሌሉ በሌላ ቀን ቀጠሮ ተይዞ ክርክሩ ይቀጥላል፡፡ - ምስክር ከጠፋ እንዲማሉ ይደረጋል፡፡ ከመሀላው በፍት እንዲማል የተፈረደበት ሰው ዘመዶቹ ድርጊቱ እንዳይማል ይመክሩታል፡፡ ፍጽሞ ከሆኔ ለብቻ ወስዶዉት፡፡
- አቤቱታ አቅራቢው አሸናፊ ከሆኔ ውሳኔ ይሳጣል፡፡
ከምስክሮቹ አቤቱታ አቅራቢው በኩል ድጋፍ ካለገኘ (ከልመሰከሩለት)ተከሳሹን አልደረስክበትም ወይም አምልጦሃል ይባላል፡፡ - የውሳኔ ሀሳቡን ለተከሳሽና ለከሳሽ ወገን ይነገራል፡፡
- በውሳኔ ቅርየተሰኘው አካል ይግባኝ ይጠይቃል፡፡
ከዚያም ቅሬታ ያቀረበው አካልን አቤቱታ በመቀበል ወደ ሌላ ሽንጎ ይወሳዳሉ፡፡ - በአስራ ስምንተኛ ደረጃ፡- የውሳኔ ድምዳሜ በፋቲሃ(በዱዓ) ይዛጋል፡፡
የቅጣት አወሳሰንና ሂደት
ከዚህ በላይ ስማቸው የተጠቀሰው አምስቱ ባህላዊ ህግ የቅጣት አወሳሰን እንደሚያስረደው በሁለት መልክ ነው፡፡
እሱም ብቀላ እና ከሳ ክፍያ ቅጣት ናቸው፡፡
ብቅላ ማለት አንድ ሰው በእሱ ላይ የተፈጸመው ድርጊት በሰው ላይ መፈጸም ማለት ነው፡፡
እነሱም "የተከላከሉ ነገሮች ፈጽሞ
መገኝትና ፈጽም የተባሉት ነገር ፋጽሞ አለመገኘት" ናቸው፡፡
በአጭሩ ብቅላ ማለት ድጋሚ ወንጀል ማለት ነው፡፡
ለምሳሌ፤- አንድ ሰው ወንድሙ የገደለበትን ጎሳ አባል ከገደለ ብቀላ ይባላል፡፡
በአፋር ባህላዊ ህግ ሰው መግደል ቢሉ(ነፍስ መጥፋት ወንጀል) ይሆናል፡፡
ነፍስ መጥፋት ወንጀል በትኩሱ በብቀላ፣ ከረገበ ደግሞ በህይወት ካሳ ክፍያ እልባት ያገኛል፡፡
ነፍስ መጥፋት ወንጀል የፈጸመ ሰው ቢዘጋይም መሞቱ አይቀሪም የሚባል አባባል አለ፡፡ በአፋርባህላዊ ህግ ብቀላ ባይበረታታም እንደ ጥፋት ግን አይታይም፡፡
ይህ ማለት ተበቀሉ ተብሎ ባይመከሪም ብቅላ ከተፈጸመ ግን አግባብ አይደለም አይሉትም፡፡ የካሳ ክፍያ ስንል በተፈጸመው ጥፋት ለጠፋው/ለወደመው ክፍያ መክፈል ማለት ነው፡፡
የሟች ቤተሰቦች ከተስማሙ ለጠፋው ህይወት ካሳ ይከፋላል፡፡
በአፋር ባህላዊ ህግ መሰረት ሰው በሰው ላይ ለፈጸመው ወንጀል ካሳ ክፍያ በሁለት ይከፈላል፡፡ የህይወት ካሳ ዲያት ሲባል በአካል ለደረሰው ካሳ ደግሞ ዲክሃ ይባላል፡፡
ካሳ ክፍያ ለእነዚህ ሁለት ነገሮች ብቻ የሚከፈል ሳይሆን እጅና እግር፣ ብልት(ዝሙት)ና ምላስ፤ ሌብነትና ቃጠሎ ለደረሰው ጥፋት ጭምር ካሳ ይከፈላል፡፡
የእግርጥፋት ወንጀሉ እንድፈጸም መንገድ መምራት 小 መጠቆም፡፡ የብልት ጥፋት ዝሙት ሲሆን የምላስ ጥፋት ደግሞ ስድብ በባህላዊ ህጉ መሰረት የካሳ
ክፍያ አላቸው፡፡
ከአምስቱ ባህላዊ ህጎች ቡርአሊ _ ህግና ከዴብኔክ-ዌኢማ ህግ ጎበኣድ ቅርንጫፍ ዉጭያሉት የክፍያ በላም የሚተመን ሲሆን በቡርኢሊ ህግ ደግሞ የካሳ ክፍያ በሴት ግልገል ይተመናል፡፡ ይሁንና ላሚም ሆኔ ግልገል ወደ ግመልም ሆኔ ወደ ብርይመነዝራሉ፡፡
አፋር ባህላዊ ህጎች እንደየ አካባቢያቸው የተለያየ ስያሜ ቢሰጣቸውም በህጉ መካከል መሰረታዊ የሆኔ ልዩነት የለም፡፡
በዚህ መሰረት ከሰው ልጅ የጥፋት መንስኤ ሊሆኑ የሚችሉት አራቱ የሰውነት አካላት መሆናቸው ላይ ይስማማሉ፡፡