የአፋር ህዝብ ባህል፣ ታሪክ፣ ባህላዊ ሕግ (Mada’a)፣ የኑሮ ዘይቤ፣ የምስል መዝገብ እና ዲጂታል መጽሐፍት በአንድ የባህል መድረክ ውስጥ።
ባህል፣ ባህላዊ ሕግ እና የምስሎች ጋላሪ በአንድ ዲጂታል ላይብረሪ።
አንባቢ ሁነታ፣ ፍለጋ፣ የይዘት ማውጫ፣ የጨለማ ሁነታ እና ለሞባይል የተመቸ አቀራረብ።
የአፋር ባህልና ቅርስ፣ ቋንቋ እና ጥንታዊ ዕውቀቶችን ለቀጣይ ትውልድ ማስተላለፍና ለሌሎች ማስተዋወቅ።
ቅርስን መዝግቦ ማቆየት፣ መጠበቅ እና ለትውልድ ማስተላለፍ።
በአፋርኛ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ተደራሽ ማድረግ።
ባህል፣ ሕግና ማንነትን ለወጣቶች በዘመናዊ መንገድ ማስተማር።
ይህ የአፋር ባህል የተሰኘው ዲጂታል መድረክ የአፋርን ታሪክ፣ ባህላዊ ህግ/ ማድዓ እና ቅርስ በዲጂታል መልክ በመሰነድ ለቀጣይ ትውልድ ለማስተላለፍ በክፍተኛ ተነሳሽነትን ተመስርቷል። ፕሮጀክቱ በአፋር ቅርስ ላይ ያተኮረ የመጀመሪያው መጠነ ሰፊ ዲጂታል የባህል መድረክ ለመፍጠር የባህል ምርምርን፣ ባለብዙ ቋንቋ ዲጂታል ኅትመቶችን፣ የማኅበረሰብ ታሪክ አተራረክን እና ዘመናዊ ቴክኖሎጂን ያጣምራል።
በዲጂታል መጻሕፍት፣ መዛግብት፣ ምስላዊ ስብስቦች እና ትምህርታዊ ግብዓቶች አማካኝነት መድረኩ የአፋርን እውቀት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተደራሽ በማድረግ የባህል ማንነትን ለማጠናከር ያለመ ነው።
የዚህ መድረክ ይዘቶች በባህላዊ ምርምር፣ በቃል ታሪክ፣ በቃለ ምልልሶች፣ በባህላዊ እውቀት፣ በማኅበረሰብ
ሽማግሌዎች፣ በመጻሕፍት፣ በአካዳሚክ ኅትመቶች እና በመስክ ሰነዶች ላይ የተመሰረቱ ናቸው።
የሀገር ሽማግሌዎች፣ ባህላዊ ህግ አዋቂዎችና መሪዎች፣ የባህል ጠባቂዎች እና የማኅበረሰብ ውይይት።
መጻሕፍት፣ የዩኒቨርሲቲ ኅትመቶች እና ክልላዊ የታሪካ ሰነዶች።
የተሰበሰቡ ምስላዊ መዛግብት፣ ቃለ ምልልሶች እና የባህል ምልከታዎች።
ልዩ ምስጋና ለአፋር ሽማግሌዎች፣ የጎሳ መሪዎች፣ ተመራማሪዎች፣ የታሪክ ምሁራን፣
የማኅበረሰብ አስተዋጽዖ አበርካቾች እና የአፋርን ማንነት እና ቅርስ መጠበቅ ለቀጠሉ ሁሉ ይድረስ።
እንዲሁም በዚህ ድህረ፡ገፅ ላይ የተሰነዱ የህላዊ ባህልና ቅርስ ጥናታዊ ስነዶችን ያስተባበሩ የ አፋር ብህራዊ ክልላዊ መንግስት
ባህልና ቱሪዝም ቢሮ (ባያነው ስያመው) በ አሁኑ የብህልና ወጣቶች ቢሮ ይህንን ባህላዊ ዕሴቶችን በመሰነዳቸው የላቀ ምስጋና ይድረሳቸው።
በመጨረሻም በተለየ መልኩ ለተባበርኝ የታሪክ ምሁሩ አቶ ሀቢብ ሙሀመድ ሀሰንን ከልብ አመስግናለሁ።
ይህ መድረክ ለወደፊቱ የአፋር ሕዝብ ትውልዶች የተሰጠ ነው።
የአፋር የቱሪዝም መዳረሻዎችን፣ መራኪ መልክዓ ምድር ገፅታዎች፣ የአፋር ህዝብ የአኗኗር ዘይቤ እና ቅርስ ቦታዎችን ለመጎብኘት የጉዞ መመሪያዎችና መረጃዎችን ይመልከቱ።
የቱሪዝም ገጽን ይክፈቱ
በምድር ላይ ካሉት እጅግ ሞቃታማ እና ልዩ ቦታዎች አንዱ።
በጨው ሀብት የታደለ፣ ለአይን ማራኪና፣ በአፋር ካሉ የቱርዝም መዳረሻዎች አንዱ